Tidarfelagi.com

ሕሩይ ሚናስ

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ታላቅ ቦታ ከያዙ ሰዎች አንዱ ነው። እስካሁን ካነበብኳቸው የአማርኛ መጽሐፍት በልዩ ኹኔታ ከማስታውሳቸው ጥቂት ሥራዎች አንዱ የሕሩይ ሚናስ “እብዱ” የሚለው ሥራ ነው። የራሱን devastating experience በመጽሐፍ መልክ በመሰነድ ለአጥኚ ባለሙያዎች ራሱ እጅግ እንቆቅልሽ የኾነውን የአእምሮ መታውክ በሽታ (schizophrenia)ን ግልጥልጥ አድርጎ ስለጻፈ ኹሌም የመጽሐፉን አብዛኛው ክፍል አልረሳም። አብዛኛው የበሽታው ምልክቶችን ይዟል “እብዱ” መጽሐፍ።

ለምሣሌ

1. positive symptoms of schizophrenia በመባል ከሚታወቁ ምልክቶሽ መካከል አንዱ
“catatonia” የሚባለው condition ነው። እሱም በሽተኛው እንግዳ በኾነ ኹኔታ አንድ ቦታ ላይ የተለየ position ኾኖ (ለምሳሌ በአንድ እግሩ፣ እጁን ራሱ ላይ ጭኖ ወዘተ…መቆም ወይም መቀመጥ) ሲቆይ ነው።

ሕሩይ እንዲህ ይገልጸዋል።

“ሶቪዬት ኅብረትና አሜሪካ ውጊያን ይገጥማሉ። አንገቴን ቀና ካደረግኩ አሜሪካ እንደምታሸንፍ፤ አንገቴን አዘቅዝቄ ከቆምኩ ደግሞ ሶቪዬት እንደምታሸንፍ ገባኝ። ስለዚህ ሶቪዬት እንድታሸንፍ ከጧት እስከ ማታው 12 ሰዓት ድረስ አንገቴን አቀርቅሬ ቆሜ ዋልኩ። ላሞቹም አጠገቤ ሲደርሱ ሥራ መያዜን አውቀው ሰላምታ ሰጥተውኝ ያልፋሉ። ማታውን ሶቪዬት አሸነፈች። በዚያውም ቀን ስምንተኛው ሺሕ ገብቶ አደረ” ይላል።

2.Hallucination

በእውኑ ዓለም የሌሉ ነገሮችን መስማት ወይም ማየት ወይም ሁለቱም። ትዕዛዝ መቀበል፣ ስድብን መስማት….ወዘተ።

ሕሩይ እንዲህ ይላል

“ሦስተኛው የዓለም ጦርነት በቻይናና ጉራጌ መካከል እንደሆነ ገባኝ። ማሪያም እንደነገረችኝ ከኾነ ይኼ ጦርነት የሚደረገው በጦር መሣሪያ ሳይሆን በካራት ነው። ስለዚህ እኔም ካራት መማር እንዳለብኝ ነገረችኝ። ፍጥነት የምታስተማረኝ መስኮት በመክፈትና በመዝጋት ነበር። እለማመድ ዘንድ ደግሞ (ሶቶችና ሕጻናትን??) እንድመታ ታዘኝ ነበር።”

አውግቸው ተረፈ በሚል የብዕር ሥሙ “ጣፋጭ የግሪም ተረቶች”፣ የዓለም ምርጥ ተረቶች” (በሦስት ቅፆች)፣ “ወይ አዲስ አበባ” እና ሌሎች መጽሐፍትን የጻፈው ሕሩይ ሚናስ ትላንት ሰኔ 10፥ 2011 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ 5ኛ ዓመት ኾነን እንደ minor ከተማርናቸው ትምህርቶች አንዱ የኾነውን psychiatry ስንማር አብዛኛውን የመጽሐፉ ክልፍ እያነበቡ ያስተማሩን ከቀደምት ኢትዮጵያዊያን የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያዎች መካከል ዶ/ር ገብረእዝጊ እና ዶ/ር ማሙዬን ኹሌም የማልረሳቸው አንዱ ምክንያት የአውግቸው ተረፈን መጽሐፍ ይበልጥ እንድረዳው ስላረጉኝ ነው።

“እብዱ” አንድ የschizophrenia ተጠቂ ሰው የሚያስታውሰውን ከሕክምና ሣይንሱ ጋር ሙሉ መሉ በሚባል ደረጀ በሚገናኝ መልኩ የጻፈው ትልቅ መጽሐፍ ነው።

ለሕሩይ ሚናስ ቤተሰቦች መጽናናቱን ተመኘሁ! ኹሌም እንደሚኮሩበት ምንም አልጠራጠርም፥ታላቅ ሰው ነበረና!

2 Comments

  • Oshoend commented on July 15, 2019 Reply

    “እብዱ”
    አዕምሮዬ ላይ ታትሞ ቀርቷል ።

  • masterandinet@gmail.com'
    Andu Mela commented on August 21, 2019 Reply

    Yes right … Awugechewu Terfe is a great man … no doubt about it. we always love him …

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...