አንተ! ንቃት መሃል የተኛህ! ጩኸት መሃል የምትናውዝ! ቀውጢ መሃል የምታንኮራፋ ንቃ!!
እዛ… በዘረኝነት ጠባብ አልጋ ላይ ተኝተህ የምትናውዝ ንቃ! እንደምን እንቅልፍ ወሰደህ ብለህ ስንደነቅ ደንገጥ እንኳን ሳትል እንክልፍህን መለጠጥ?? ኸረ ንቃ!!
የመታከት አየር እየሳብክ፣ መታከት የምትተነፍስ አንተ ንቃ! አይንህን ግለጥ! አዕምሮህን ግለጥ! …. ነብስህ የሸበተብህ አንተ! የነብስህን የሸበቱ ነጫጭ ፀጉሮች ለመደበቅ ጥቁር ሽንገላ በአፍህ ይዘህ የምትዞር አንተ ሰው ንቃ!! በንቃት መሃል ተኝተሃል! ከዓለም ሁሉ ተለይተህ አንቀላፍተሃል!
አዕምሮህን የታሳቡ ሃሳቦችን አሜን ብሎ ለማስቀበል እንጂ ለማሰብ እድል …. ነብስህ የሸበተብህ አንተ! የነብስህን የሸበቱ ነጫጭ ፀጉሮች ለመደበቅ ጥቁር ሽንገላ በአፍህ ይዘህ የምትዞር አንተ ሰው ንቃ!! በንቃት መሃል ተኝተሃል! ከዓለም ሁሉ ተለይተህ አንቀላፍተሃል!
አዕምሮህን የታሳቡ ሃሳቦችን አሜን ብሎ ለማስቀበል እንጂ ለማሰብ እድል የማትሰጥ አንተ…. ኸረ ተው ንቃ!…….. ለመኖር በሚል አንካሳ ሽንገላ፣ እራስህን አሻሽጠህ የገዢዎችህ ሃሳብ ማስወገጃ የሆንክ አንተ ሰው ንቃ!!
“ምሁርነት” የሚል ጉብታ ላይ ቆመህ፣ ገደል ውስጥ ከቆመው “ተራ ሰው” አንሰህ የምትታይ አንተ….ንቃ! በንቃት መሃል ተኝተሃል!!
“በምን ቸገረኝ” የብቻህን እንቅልፍ ፈጥረህ፣ በጋራችን አልጋ ላይ እንቅልፍህን የምትለጥጥ አንተ ሰው ንቃ! …. ከራስህ ጉድለት ይልቅ የሰው ሙላት የሚያጎድልህ አንተ ሰው ንቃ!
እንካ ተጋበዝ አንድ ጥቅስ! ፀሐፊው ኦታም ፑልቶ(ስንቅነህ እሸቱ) ይባላል። መቼም ተኝተሃል ምን ጊዜ አግኝተህ ታነበዋለህ?! እንዲህ ይልሃል፤
“ተራምደህ ዱካህ የማይታይ ከሆነ መሰለህ እንጂ አልተራመድክም። ኖረህ ትውስታ ካልተውክ መሰለህ እንጂ አልኖርክም”(133)
ተነስ አንተ ዱካህ የማይታይ! እያለህ የሌለህ አንተ ተነስ! መንገድህን ንፋስ የሚያቀናልህ አንተ የንፋስ ሎሌ ንቃ! …ነቃ በል!! ሀገርህን በአንድ ሰው እንቅልፍ ሰበብ ያስቀደምክ አንተ…. ተነስ!!
…….ጃስስ!!
One Comment
ante.ye ewnet ayn aleh ,….