Tidarfelagi.com

ሀገሬ ታማለች!

ታማሚ የመሆንሽን እውነት፣
ስታውቂው፣ ሳውቀው ሳይርቀን፣
ለምን ነው፣ ይህ አባይ ቃልሽ እውነቱን የሚደብቀን?

ልንገርሽ አይደለ እውነት….
እንዳንቺም ታማሚ የለ
በምድር የተስተዋለ
አንድነት ቁስል ሆኖበት
ልዩነት ደዌ ፀንቶበት፣
መንገዱን ለሞት ያበጀ
ፍፃሜን በራ ያወጀ
እንዳንቺም ታማሚ የለ፣
በምድር የተስተዋለ፡፡
ግራሽን ለመታ ሁሉ፣ ቀኝሽን እየሰጠሽው፣
መጠፍጠፍ፣ መንጠፍ ልማድሽ፣ የቱን ነው ጤና ነኝ ያልሽው?
የቱ ነው ያንቺ ጤንነት፣ “ጤና ነኝ!” የሚባልበት?!
አንድነት ከተነቀለ
ልዩነት ካጎነቆለ
መራራቅ አርቡ ከሰፋ
መናናቅ አቅሙ ከከፋ
ጤንነት ምንድን ነው ውሉ
ትርጉሙ ላንቺ የጠፋ?
አታብይ ሀቁ ይነገር፤
ማበሉ ካልተቀየረ
መድሃኒት ህልም ነው ትልሙ- ህመሙ ካልተነገረ
እና እናገራለሁ፣ ሀገሬ ታማለች!

የራስ የሚያስጠላ፣ የሰው የሚያስወድድ
ከራስ የሚያጣላ፣ ለሌላ `ሚያሰግድ
ትውልድ የሚነክል የጭንቅላት እጢ ከአዕምሬዋ ገብቶ
ያባክናት ይዟል እጅ እግሯን ቀፍቶ

ሃገሬ ታማለች! ሊገድላት ነው ህመም
አዳኝ ልጇ ደርሶ፣ አይቷት ሳትታከም
ሀኪም ባገር የለም አዳኝ እርቋታል፣
ህመሟ ይሄን አይቶ አጉል ከፍቶባታል፡፡

መታመሟን ያዩ ልጆቿ እየሸሽዋት፣
ህመሟ እየፀና፣ ጉልበት እየከዳት፣
ጤና ነኝ ለማለት በውሸት ብትፈግግም
አስተውሎ ላያት ሀቁ አይሸሸግም፡፡
ሃገሬ ታማለች….

መታመሟን ያዩ፤
ምናችን ሞኝ ነው፣ ቂሎች ይሸወዱ
እያሉ ተናግረው፣ ጥለዋት ነጎዱ
እኛ “ሞኞቹ” ላይ፣ ክንዳችን ላይ ታማ
በአምሮት ያያታል ሞት፣ በአጉል ዘመን ታማ፡፡
መድሃኒት አግኝተው፣ ማዳን ከማይችሉ፣
ጥለዋት የሸሹት “ብልጦቹ” ተሻሉ፡፡

ሀገሬ ታማለች….
ፈረንጅ በሽታ፣ ሀገረኛ ህመም
የራስን የመጣል ወደ ሌላ መዝመም
ተከፋፍሎ ማሰብ፣ ተነጣጥሎ ማሰብ
ድብልቅልቅ ቁርጥማት፣
የታሪክ ስብራት……
እየቀሳሰፈ፣ እየቆላለፈ
ጤናዋ ተናጋ፣ ህመሟ ተረፈ፡፡
ህመሟ የገባቸው፣ ጤናዋ እንዲመለስ የፈለጉ ሁሉ
መድሃኒት ፍለጋ ሰማይን ይቧጭሩ-
መሬት ይቆፍሩ
አሊያ ይተዉት፣ አሻፈረን ካሉ፣
ስትሞት በሞታቸው ይገላገላሉ!!

የራስ ናቸው፡፡ የማንንም ሃሳብ ለመፃፍ አልተከፈተም! የሚያስማሙንን ሃሳቦች እዚህ ካገኛችሁ እሰየው፡፡ ለመስማማት አንፅፍም፣ ለመፃፍ አንስማማም፡፡ ወዘተ

One Comment

  • wondwosen.k2245@gmail.com'
    ወንድወሠን commented on May 29, 2018 Reply

    ደሥ የሚል ግጥም ነው

አስተያየትዎን እዚህ ይስጡ

የኢሜል አድራሻዎ አይወጣም

Loading...