ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት

ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው jራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድርማንበብ ይቀጥሉ…

ጠላታችን ሥም ነው!

ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ሕዝባዊ ሥነ-ቃሎቻችንን በጨረፍታ

የኛ ሕዝብ ሲከፋውም ሆነ ሲደሰት ሥነ-ቃሎችን ተጠቅሞ ብሶቱን፣ ችግሩንና ደስታውን ይገልፃል። ጉልበት ኖሮት በትር ባይወዘውዝም፣ ዘገር ባይነቀንቅምና ጠመንጃ ባይወድርም፣ ተንኳሹን፣ በዳዩን ወይም አጥቂውን ወገን በሥነ-ቃል ያለፍራቻ ያወግዛል። ይሄን ሲያደርግ እታሰራለሁ፣ እገረፋለሁ ወይም እሰቀላለሁ የሚል የፍራቻ ስሜት ልቡ ውስጥ ሽው የሚልበትምማንበብ ይቀጥሉ…

ወዛደር እና ወዝውዞ አደር

በቀደም አንድ የተባረከ ዜጋ “የዶሮ በሽታ ገብቷል” ሚል ወሬ ነዝቶ የእንቁላልን ዋጋ ቁልቁል ወሰደው፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከርኩ፤ የቤት ሰራተኛየ “ዛሬ ምን ይሰራልህ?” ስትለኝ “ ቆንጆ ሽሮ አንተክትኪልኝና አንድ አምስት የተቀቀለ እንቁላል ጣል አርጊበት” እላታለሁ፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የሆነ ክሊኒክ ምርመራማንበብ ይቀጥሉ…

የአጎቴ አነቃቂ ንግግሮች እና የእኔ መፍዘዝ!

እንደማንኛውም ዕድሜው ለማትሪክ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ፣ ዩኒቨርሲቲ የመግባትና ተመርቆ የመውጣት ዕድል ገጥሞኛል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ አጎቴ ብዙ ምክርና ትንሽ የኪስ ገንዘብ በመላክ እያማረረ አስተምሮኛል። (አጎቴ ግን ለሰዎች ሲናገር “እያዝናናሁ አስተማርኩት” ነው የሚለው) የሚልክልኝ ብር በጣም ከማነሷ የተነሳ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ካለመድረስ መድረስ!

አያልቅ የብሶት ገጽ ወዴትም ብንገልጠው፣ ሐዘን መጻፍ ነው ወይ ለኛ የተሰጠው ? አያልቅ የቀን መንገድ -ብንሄደው ብንሄደው፣ ፈቀቅ አይል ጋራው- ብንወጣ ብንወርደው፤ ረቂቅ ግዝፈቱ አይፈርስም ብ’ንደው፣ በ’ሳት ሰረገላ ሰማዩን አንቀደው! ምን ቢጠቁር ቆዳው -ምን ቢነጣ ፊቱ፣ ምን ቢሞላ ጓዳው- ቢራቆትማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንዱ መፅሐፍ …

ልድገመውና …ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በፈረንጆቹ 1936 አንዲት ማርጋሬት ሜሸል የተባለች አሜሪካዊት ጋዜጠኛ እግሯን ወለም ብሏት አልጋ ላይ ዋለች …ታዲያ ስብራቷን እያዳመጠች ከማለቃቀስ ይልቅ በደጉ ጊዜ አእምሮዋ ውስጥ የተጠራቀመውን የአገሯን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መፃፍ ጀመረች … እንዲሁ በደረቁ ሳይሆን እንደኛውማንበብ ይቀጥሉ…

የወንዶች ሳሎን

በቀደም ዳጎስ ያለ ደመወዝ ተቀብየ ፥ ነጠር ነጠር እያልሁ በሰፈራችን ሳልፍ፥ “በውቄ ግባና ጸጉርህን ትንሽ ላሰማምርልህ “ የሚል ድምጽ ሰማሁ፤ የብዙ ዘመን ጸጉር አስተካካየ ሳሚ ነው ፤ ሚካያ በሐይሉ ‘ ጸጉሬንም ቆጥረሀል “ ብላ የዘፈነችው ለሳሚ ይመስለኛል፤ ሳሚ ፈጣን ነውማንበብ ይቀጥሉ…

ቀውስጦስ የት ነው?

ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገትማንበብ ይቀጥሉ…

ሰሞንኛ ጨዋታ

ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ውስጥ በሚገኘው የ”አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼማንበብ ይቀጥሉ…

የሽግግር መንግሥቱ ትውስታ በጥቂቱ (1983-1987)

ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረውማንበብ ይቀጥሉ…

EPDA – በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት

የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታንማንበብ ይቀጥሉ…

ሽልማቱ

“በምርጥ ነጠላ ዜማ ዘርፍ ያመቱ ኮከብ ተሸላሚ ማሞ መንገሻ “ ብሎ ለፈፈ ፥ የመድረክ መሪው አዳራሹ በጭብጨባ ተርገበገበ የማሞ ልብ በሀይል መምታት ጀመረ፥ ተሸላሚነቱን ከሰማ ጊዜ ጀምሮ መኪና እሸለማለሁ የሚል ሰመመን ጭንቅላቱን ተቆጣጥሮት ቆይቷል፤ ምን አይነት መኪና ይሆን እሚሸልሙኝ የሚልማንበብ ይቀጥሉ…

የተካደ ትውልድ

የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍትማንበብ ይቀጥሉ…

አቦሌ

ከማውቃቸው ሰዎች መሀል በነውጠኝነቱ ወደር የሌለው አቦሌ ነው፤ ከብዙ ጊዜ በሁዋላ አንድ የጫማ መሸጫ ቤት ውስጥ ሳገኘው ገረመኝ፤ በፊቱ ያለው ውስብስብ ሰንበር የቀለበት መንገድ ይመስላል፤ ግንባሩ ላይ የብረት ቦክስ ጠባሳ አለ፤ ግራ ጉንጩ ላይ የሰንጢ ጭረት ይታያል፤ ማላመጫው ግድም የኮብልስቶንማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሃያ ሁለት)

(የመጨረሻው ክፍል) «ዶክተር ራሴን ሀኪም ቤት ካገኘሁት አልድንም ይብስብኛል እመነኝ! ትንሽ ቀን አይተኸኝ ከባሰብኝ ቃል እገባልሃለሁ ራሴው ሄዳለሁ» አልኩት። ከህክምና ጣቢያ ህክምናዬን መከታተል እንዳለብኝ ሲነግረኝ እቤቱ ይዞኝ ሄደ። በዚህ ጊዜ እንዳለፈው ለማላውቀው ጊዜ ያህል ጨለማና ፍርሃቴ ውስጥ አልነከርም!! አስፈሪው ደቂቃማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ አንድ)

ፅፎ እስኪጨርስ እረፍት አጣሁ። አስሬ ላይብረሪ እመላለሳለሁ። ጣቶቹ አሁንም 100% ስላልሆኑ ቀስ ብሎ ነው የሚፅፈው። «እሺ የፃፍከውን ላንብበውና ትቀጥላለህ?» እለዋለሁ። «አይሆንም ህፃን አትሁኚ!» ይለኛል። «ጮክ ብለሽ አታንብቢልኝ! የምትጠይቂኝ ነገር ከሌለ በቀር! ለራስሽ አንብቢው» ብሎኝ ሶፋው ላይ አጠገቡ እንድቀመጥ በእጁ እየመታማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ)

እና ሰዓት ብላችሁ ከመነጫነጫችሁ በፊት ይቅርታ ብያለሁ!! ሜሪ ፈለቀ ከማይታይ ፊርማጋ ) «ትናንትህ ላይ በበደሉህ ሰዎች ነው ዓለምን በሙሉ እየዳኘህ ያለኸውኮ! በዙሪያህ ያሉ ሰዎች በሙሉ እንደእነሱ ናቸው ማለት አይደለም! በተቃራኒው የሆኑ ሰዎች አሉ። አንተ ያደረግከው ለማንም ምንም እድል አለመስጠትን ነው።»ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ዘጠኝ)

«ማዕረጌን ከጎኔ አድርጌ የተጋበዝነውን እራት ልንታደም ስንሄድ ዘውድ እንደተደፋለት ልዑል አንገቴን ቀና አድርጌ በኩራት ነበር። ምንም የጎደለኝ ነገር አልነበረም። ማዕረጌ ከጎኔ ነበረቻ!! ከሶስት ሳምንት በኋላ እሷ እንደተመኘችው በሷው አባባል <እልልልልልልል በተባለለት ሰርግ> ወዳጅም ጠላትም ምስክር ሆኖ ባደባባይ የእኔ ልትሆን ነዋ!!ማንበብ ይቀጥሉ…

ኑሮ እና ብልሀቱ

የወሎ መንፈስ አድናቂ ነኝ፤ ስለወሎ ሲነሳ ይቺ ወግ ትዝ ትለኛለች፤ አንድ ሼህ እና አንድ ቄስ ወደ መስጊድ እየሄዱ ነው፤ ምንም አገሩ ወሎ ቢሆን ቄስና ሼህ ባንድ ላይ ወደ መስጊድ ሊሄዱ አይችሉም ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ እሺ በቃ ፥ ቄሱ ሼሁን ወደ መስጊድማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስምንት)

«ታውቂያለሽ የአዕምሮ ክፍላችን እድገት በ25 ዓመታችን እንደሚያበቃ? ከዛም ውስጥ ከ80% በላዩ የሚያድገው እስከ 5 ዓመት አካባቢ ባለው እድሜያችን ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ልጅ ከ25 ዓመቱ በፊት በሚያዳብረው ልምድ ፣እውቀት ፣ ባህል ፣ ሀይማኖት ……. Whatever ነው የሚቀረፀው። ልክ አለመሆኑን ቢያውቅማንበብ ይቀጥሉ…

ምንሽን

የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፥ በወጣሁበት እንዳልቀር አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፥ ግና ምንድር ነው ማፍቀር እንዳስመሳይ አዝማሪ፥ ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስከዛሬ፥ ከጣቶችሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መቸ ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ፥ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሰባት)

«አንተ እረፍ ልመለስ! ያወቀ እንደሆነ ደግሞ ዲዳ ሆኖ ሀሁ ሳስቆጥረው ልክረም?» የሚለውን ሳቃቸው ያጀበውን ድምፅዋን ነው። ሳቃቸውን ሳይጨርሱ ብቅ ሲሉ መንቀሳቀስ አቅቶኝ እንደቆምኩ ነበር። > የሚለውን እንደፃፍኩ አቁሜ « በመድሃንያለም !ውይ ምን ሆና ነው?» አልኩኝ ራሴው ቁዝም ብዬ «ሰው! ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስድስት)

«ስድስት ዓመት ሙሉ ምን ዓይነት ቀኖች እንደነበሩህ ለአንባቢ ምንም ፍንጭ ሳትሰጥ 20 ዓመትህ ላይ ወደ ሆነ ታሪክ መሄድ ታሪኩን አያጎድለውም?» «ምንም የሚፃፍ ታሪክ የለውም። ፊልም ቢሆን (በጭንቅላቱ ምስሉን እየከሰተ) ምን ዓይነት ትራንዚሽን መሰለሽ? ማታ 14 ዓመቱ ላይ ተኝቶ ጠዋት 20ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አምስት)

ሲመስለኝ ፍቅርም ይረታል። በቁጣ ፣ በክፋት እና በበቀል ይረታል። ወይም ምናልባት እሱን ከማይመስሉ ባህርያት ጋር ግብ ግብ አይገጥም ይሆናል እና ቦታ ይለቃል። ቀስ በቀስ ቁጣ እና መከፋቴ ፍቅሬን እየሸፈነው መጣ። እዚህ ነጥብ ላይ የማስበው ሁሉ በምን መንገድ እኔን ማጣቱ እንዲቆጨው፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አራት)

«ታዲያ ቢያንስ ልታሳውቂኝ አይገባም ነበር? እኔ ምን አግብቶኝ ነው የአባትሽን ቁማር ቅሌት የምሸፍነው? ከዛሬ በኋላ ከገንዘቤ ላይ በዚህ ሰበብ ቤሳቤስቲን እንዲነሳ አልፈልግም።» አለኝ የብዙ ሰዎች ባህሪ መሰለኝ። እየተገፋን እና በፍቅር የወደቅንለት ሰው በማይገባን መልኩ ክፋትና ጥላቻ እያሳየን ያየነውን መመዝበር አምነንማንበብ ይቀጥሉ…

ያ’መት በዓል ማግስት ትእይንቶች

የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥ የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለውማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሶስት)

«ሁሉም ሰውኮ አንድ የሆነ ስስ የሆነበት ጎን አለው። ሰዎች ስስ ጎንህን ማወቃቸው ሁሌም መጥፎ ነገር አይደለም። በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ድክመትህን ለመጥፎ ቀን አንተን ለመጣያ ጥይት አድርገው ሊጠቀሙበት ያስቀምጡታል። ለማን ምን ልንገር የሚለው ይመስለኛል እንጂ የሚወስነው ………..» ከአፌ ነጥቆኝ ቀጠለ «ሁሉምማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሁለት)

«ዝናቡ ፀቡ ከምሽቱ ጋር ይሁን ከእርሱ ጥበቃ ጋር አይገባውም። የጠቆረው ሰማይ እያፏጨ ያለቅሳል። ……… » «የመብረቁ ብልጭታ ምናምን ምናምን ብለህ አትቀጥልማ?» ከት ብሎ ሳቀ በድጋሚ ሌላ ቀን ባዮግራፊውን ልንፅፍ ተቀምጠን ነው ከምን እንደምንጀምር ላልቆጠርነው ጊዜ የምንጀምር የምንሰርዘው። ዛሬ ባልተለመደ ሁኔታማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አንድ)

እሱን ዞሬ አየሁት! መልሼ እነሱን አየሁ! እግሬ መቆም አቃተው! ዘሎ እጆቹን ከስሬ ሲያነጥፋቸው፣ እጁ ላይ ራሴን ስጥል፣ አይኔ ከመከደኑ በፊት ከጉሮሮው የማይወጣ ጩኸት እያማጠ ሊጮህ ሲታገል አየዋለሁ። ስቃይ ያለበት ፊት………. ሰከንዶች ወይ ደቂቃ አላውቅም እጁ ላይ ምንያህል እንደቆየሁ ግን እንደነበርኩማንበብ ይቀጥሉ…

የሚያሳስበኝ

ይሄ ጨዋታ አይደለም፥ በቀደም ከሜክስኮ ወደ ፒያሳ የሚያወጣውን የቸርቺል አቀበት ስወጣ ሁለት ጎረምሶች ከግራ ቀኝ አጀቡኝ፤ አንዱ ናፕኪን እንድገዛው ጠየቀኝ ፤ ቸል ብየው ተራመድሁ፤ ከቀኘ ያለው ጎረምሳ ክንዴን አፈፍ አድርጎ ይዞ “ብራዘር ርቦኛል የዳቦ መግዣ ስጠኝ” አለኝ፤ ጣቶቹ ክንዴን ላይማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት ….. እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስር)

«የእናቱን ለቀናት የቆየ የሚሸት ሬሳ ታቅፎ ከጎሮሮው የማይወጣ ጩኸት ጮኸ። ድምፁ ከጉሮሮው እንደማይወጣ ቢያውቅም በሆነ ተዓምር የሆነ ሰው እንዲደርስለት ተመኘ። በማይሰማ ድምፅ ሊደርስለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ስላወቀ አይኞቹን ጨፍኖ <አምላኬ ሆይ እባክህ ድረስልኝ? እባክህ ድረስልኝ? እባክህ? ……… > እያለማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ዘጠኝ)

«እኔ ከዚህ በላይ ማስመሰል አልችልም! ከአቅሜ በላይ ነው የምወድህ!» እያልኩት እናቱ ናፍቃው እንዳገኘ ህፃን መንሰቅሰቅ ጀመርኩ። የሚያስለቅሰኝ ምኑ እንደሆነ ለራሴ ምክንያት መስጠት አልቻልኩም። ፍቅሩ፣ ፍርሃቴ፣ ሳልናገር መታፈኔ ……… አላውቅም። እንደህፃን ድምፅ አውጥቼ እዬዬ ማለት ጀመርኩ። እሱ መጀመሪያ እየከወነ ያለውን ልፋትማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ስምንት)

ጥፋቴ ማፍቀሬ ነበር አላልኳችሁም? የትኛው ዓመት ፣ መቼ ላይ እንዳፈቀርኩት እንኳንኮ አላውቅም! ቀስ በቀስ ……. መሰረቱን ሲጥል ….. ግድግዳውን ሲገነባ ….. ጣራውን ሲከድን …… ቀለም ሲቀባባባ ፣ ወለሉን ሲያሳምር …… ገዝፎ ገዝፎ ተሰርቶ አልቆ …… በአራተኛው ዓመት በራሴ ላይ ማዘዝማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሰባት)

ሰርጉ የራሴ ሆኖ ፣ በሰው ሰራሽ ፋብሪካ የተመረተ ሮቦት ይመስል ዘመድ አልባ ባል ላገባ የተዘጋጀሁት እኔ ሆኜ ሳለሁ፣ ሰርጉ ላይ ሚዜ እንኳን የሚሆን ጓደኛ የሌለው ባል ለማግባት ራሴ አምኜ ………. ምን ይሉ ይሆን ብዬ የምጨነቀው ለቤተሰብ ፣ ሰርጉ እንከን እንዳይኖረውማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ስድስት)

የዛን ቀን …….. እንኳን ዶክመንተሪ ፊልሙን አይተን ስንጨርስ በሙቀቱ ወዝቶ ቅባት የተቀባ የመሰለውን ጠይም ፈርጣማ ደረቱን እጄ ሲንቀለቀል ሄዶ የነካው ቀን……… እጄን ደረቱ ላይ በእጁ ደግፎ እንዳላንቀሳቅሰው ይዞት «እርግጠኛ ነሽ?» «ቨርጅን አይደለሁምኮ።» «አውቃለሁ!! በኋላ የፀፀትሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም።» እያለኝ ትንፋሹማንበብ ይቀጥሉ…

አሳዳጅ

የኑሮ ውድነት የማያሳስባቸው ነዋሪዎች ፥ ደላላ፥ የመሬት ሽያጭ ሰራተኛ ፥ ሰባኪ ፥ ታዋቂ ዘፋኝ እና አነቃቂ ንግግር አቅራቢ ናቸው፥ ባለፈው አንድ የታወቀ አነቃቂ ነኝ እሚል ሰውየ ላስር ደቂቃ አፉን ያለገደብ ወለል አድርጎ ከፍቶ ሲያዛጋ አየሁት፥ ጠጋ አልሁና ”በውኑ ከዚህ አፍማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አምስት)

«እኔ ደስ የሚለኝ ጓደኛሞች ብንሆን ነው።» አልኩት እቤቱ ይዞኝ የሄደ ቀን «እረፊ! እኔ አንዴ ልብስሽን አውልቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ስዬሻለሁ። ጓደኛሞች እንሁን ብልሽ ውሸቴን ነው። ገና ሳይሽ የቀሚስሽን ሶስት ትንንሽዬ ቁልፎች ፣ ቀጥሎ ዚፑን …….. ወደታች ባወልቀው ወይ ወደላይ የቱ ይፈጥናል?ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አራት)

ለመጀመሪያ ጊዜ በተያየን በአስረኛው ደቂቃ ነው <ላግባሽ> ያለኝ። የሶስተኛ ታናሼን ሰርግ ልታደም አንደኛው የከተማችን ሆቴል ነበርኩ። የምሳ ቡፌ ከተነሳ በኋላ ማንም ሳያየኝ ከአዳራሹ ውልቅ ብዬ እዛው ህንፃ ላይ ያለ ሬስቶራንት ውስጥ ገባሁ። ቢያድለኝኮ የአክስቶቼን ውግምት የሆነ ዓይን መሸሼ ነበር። ገናማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሶስት)

ከሳምንታት በኋላ ዝም አለ። በቃ ዝም! በእኔ ቁጥጥር ስር መሆኑን ላለመቀበል መፍጨርጨሩን ተወው። የእኔ እርዳታ የሚሰጠውን የተሸናፊነት ስሜት ላለመዋጥ የሚያደርገውን መንፈራገጥ ተወው። ሳጎርሰው ከምግቡ ጋር የሚውጠውን እልህ ተወው። ሰውነቱን ሳጥበው ከጡንቻው ጋር የሚያፈረጥመውን ትዕቢት አተነፈሰው። መለፍለፉንም ተወው። ዝም ጭጭ አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሁለት)

ከእኔ በፊት ሁለት ሚስት አግብቶ እንደነበር ሳላውቅ አይደለም ያገባሁት። አውቅ ነበር። ለሁለቱም ሚስቶቹ ልክ ከእኔ ጋር እንዳደረገው የሀብት ውርስ ኮንትራት አስፈርሟቸው እንደነበርም አልደበቀኝም ነበር። በፍቅሩ ነሁልዬ ከእኔ በፊት የነበረው ህይወቱ ገሀነም እሳት ጭስ ሳይሸተኝ ቀርቶም አይደለም። ወይም ፍቅሬ አቅሉን አስቶትማንበብ ይቀጥሉ…

እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!

ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)

«ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?»ማንበብ ይቀጥሉ…

የተሳሳተ

ከምኡዝ ጋራ ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ተገናኘን፥ “ ከመንገድ ዳር ካለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን አቧራና ቡና እየጠጣን አላፊ አግዳሚውን እያየን እናወራለን፥ ድንገት አንዲት ሴት ብቅ አለችና ወደ ምኡዝ እያየች “ አንተ አለህ?” ብላ ባድናቆት ጮኸች፤ ሁለት እጆቿን በሰፊውማንበብ ይቀጥሉ…

ከአበታር ወደ አባተ

አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮችማንበብ ይቀጥሉ…

Loading...